🙌🙌 በBlack History Month በዚህ February ወር ላይ ከሚታወሱና ክብር ከሚሰጣቸው ውስጥ ታላቁ ኢንጅነር አያና ብሩ አንዱ ናቸው 🙌
የታላቁ የአማርኛ ታይፕራይተር የፈጠረ አባት ኢንጅነር አያና ብሩ በግንቦት 1939 ዓ/ም በጽሑፍ መኪና ለመጀመሪያ ጊዜ በስነ ጥበብ ሚኒስቴር ተፈቅዶ ጽፎ ታትሞ ያወጣው ይህ ጽሁፍ ነበር። ይህንን የመጀሪያ በጽሁፍ መኪና የታተመውን ጽሁፍ አንቡት። The father of modern Ethiopia Typography ኢንጅነር አያና ብሩ ይባላል ትውልድና እድገቱ በወለጋ ሆሮ ጉድሩ ነው:: በ1930ዎቹ (1932 G.C) የመጀመሪያውን የአማርኛ ታይፕራይተር የፈጠረ ምሁር ነበሩ። ኢንጅነር አያና ኦሊቬቲ ከተባለ የጣሊያን ካምፓኒ ጋር ለ 40 አመታት ያህል ሰርቶ ነው ይህንን የአማርኛ ታይፕራይተር ግኝትን እውን ማድረግ የቻለው። የመጀመሪያዋ ኢንጅነር አይን ብሩ የሰሯት የአማርኛ ታይፕራይተር በብሄራዊ ሙዜም ውስጥ ትገኛለች።
የኢትዮጵያን ስክሪፕት ለአሁኑ ትውልድ ያስተዋወቀ በመሆኑ የዘመናዊ ታይፖግራፊ አባት (the father of modern Typography) የሚል ስም ተሰጥቶታል።ልጃቸው ኮሌኔል አበራ አያና በደርግ ዘመን የአዲስ አበባ ፖሊሰ ዋና አዛዥ የነበሩና በኢትዮጵያ ውስጥ የማረሚያ ቤት ስርዓቶችንና የህግ ታራሚዎችን አያያዝ የቀየሩ ታላቅ ሰው ነበሩ ። ባሻዩ ታላቁ ኢንጅነር አያና ብሩ ተመራምረው የአማርኛ ፊደል ታይፕራይተር ባይፈጥሩ ኑሮ ዛሬ ላይ አዳሜ የአማርኛ ታይፕራይተር ኪቦርድ ላይ ባልፃፍሽ ነበር። የሚያሳዝነው ይህንን በፈጠሩ ታላቅ ሰው ላይ ስንት የዘረኝነት ቅርሻት የሚያቀረሹ ሁሉ አሉ ። በነገራች ላይ ኢንጅነር አያና ብሩ በ1938 ታይፕ ሙከራ ያደረጉበት የዋናው ኮፒ በ1950 የፊደል ሰራዊት በክቡር ጀኔራል ታደሰ ብሩ በሚመሩት ያሳተመው አንድ ቅርስ እጀ ላይ ይገኛል።
ስም ከመቃብር በላይ ነው ክብር ለሚገባው ክብር እንስጥ!
Negash Qemant